ማርቆስ 10:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት!” አለ፤ እነርሱም ዕውሩንም “በል በርታ! ተነሥ! ኢየሱስ ይጠራሃል!” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ቆም ብሎ፣ “ጥሩት” አላቸው። እነርሱም ዐይነ ስውሩን፣ “አይዞህ፤ ተነሥ፤ ይጠራሃል!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ቆም ብሎ፥ “ጥሩት” አላቸው። እነርሱም ዐይነ ስውሩን፥ “አይዞህ፤ ተነሥ፤ ይጠራሃል” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት” አለ። ዕውሩንም “አይዞህ፤ ተነሣ፤ ይጠራሃል፤” ብለው ጠሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ቆመና፦ ጥሩት አለ። ዕውሩንም፦ አይዞህ፥ ተነሣ፥ ይጠራሃል ብለው ጠሩት። |
በዚያም ሰዎች በአልጋ ላይ የተኛ አንድ ሽባ ይዘው ወደ እርሱ መጡ። እርሱም እምነታቸውን አይቶ፥ ሽባውን፥ “ልጄ ሆይ! አይዞህ፤ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።
ስለዚህ በሁሉም ነገር እንደ ወንድሞቹ መሆን ነበረበት፤ በዚህ ዐይነት የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ብሎ እግዚአብሔርን ለማገልገል ታማኝና መሐሪ የካህናት አለቃ ሆነ።