ማርቆስ 10:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀሩት ዐሥሩ ይህን ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ላይ ተቈጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሥሩ ይህን ሲሰሙ፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን መቈጣት ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥሩ ይህን ሲሰሙ፥ ያዕቆብንና ዮሐንስን መቆጣት ጀመሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥሩም ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ይቈጡ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሥሩም ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ይቈጡ ጀመር። |
ኢየሱስ ሁሉንም ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “የአሕዛብ አለቆች የሕዝብ ገዢዎች ተብለው እንደሚጠሩና መሪዎቻቸውም በእነርሱ ላይ ሥልጣን እንዳላቸው ታውቃላችሁ፤
በትሕትና ተሞልታችሁ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ አድርጋችሁ ቊጠሩ እንጂ በራስ ወዳድነት ወይም “ያለ እኔ ማን አለ” በሚል ትምክሕት ምንም ነገር አታድርጉ።