ስለዚህ ተማሪ እንደአስተማሪው፥ አገልጋይም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። የቤቱን ጌታ ‘ብዔልዜቡል’ ብለው ከጠሩት ቤተሰቦቹንማ ከዚህ በከፋ ስም እንዴት አይጠሩአቸውም!
ማርቆስ 10:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “አዎ፥ እንችላለን፤” አሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእርግጥ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “አዎን እንችላለን” አሉት። ኢየሱስም፣ “እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “አዎን እንችላለን” አሉት። ኢየሱስም፥ “እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም “እንችላለን፤” አሉት። ኢየሱስም “እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ እንችላለን አሉት። ኢየሱስም፦ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፥ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤ |
ስለዚህ ተማሪ እንደአስተማሪው፥ አገልጋይም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። የቤቱን ጌታ ‘ብዔልዜቡል’ ብለው ከጠሩት ቤተሰቦቹንማ ከዚህ በከፋ ስም እንዴት አይጠሩአቸውም!
ጴጥሮስ ግን “መሞት እንኳ ቢያስፈልግ ከአንተ ጋር እሞታለሁ እንጂ ከቶ አልክድህም!” እያለ አጠንክሮ ተናገረ። የቀሩትም ደቀ መዛሙርት እንዲሁ ይሉ ነበር።
እንዲህም አለ፤ “አባት ሆይ፥ ሁሉ ነገር ይቻልሃል፤ ይህን የመከራ ጽዋ ከእኔ አርቅልኝ፤ ነገር ግን እንደ አንተ ፈቃድ እንጂ እንደ እኔ ፈቃድ አይሁን።”
አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል፤ አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጐደለብኝን በሥጋዬ አሟላለሁ።
በኢየሱስ ክርስቶስ የመከራውና የመንግሥቱ እንዲሁ የትዕግሥቱ ከእናንተ ጋር ተካፋይ የሆንኩ እኔ ወንድማችሁ ዮሐንስ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ታስሬ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርኩ፤