በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ “አባትና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም “እሺ፥ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም!” ሲል መለሰለት።
ማርቆስ 1:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወዲያውኑ ጠራቸው፤ እነርሱም አባታቸውን ዘብዴዎስን ከሠራተኞቹ ጋር በጀልባው ላይ ትተውት ኢየሱስን ተከተሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዲያውኑ ጠራቸው። እነርሱም አባታቸውን በጀልባው ላይ ከቅጥር ሠራተኞቹ ጋራ ትተው ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያውኑ ጠራቸው። እነርሱም ከቅጥር ሠራተኞቹ ጋር አባታቸውን በጀልባው ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዲያውም ጠራቸው፤ አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዲያውም ጠራቸው አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ። |
በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ “አባትና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም “እሺ፥ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም!” ሲል መለሰለት።
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም።
ከዚያም ጥቂት አለፍ እንዳለ፥ ሌሎች ሁለት ወንድማማችን አየ፤ እነርሱም የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ ነበሩ፤ እነርሱ በጀልባ ላይ ሆነው መረባቸውን ይጠግኑ ነበር፤
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ብሎ ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም እናትን ወይም አባትን ወይም ልጆችን ወይም ርስትን የሚተው ሰው ይበልጥ ያገኛል፤
“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም።