በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይፈርስና ግዛቱም በሌላ ሕዝብ የማይደፈር መንግሥትን ይመሠርታል፤ ይህ መንግሥት ሌሎችን መንግሥታት እስከ መጨረሻው ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤
ማርቆስ 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሲያስተምርም፦ “ዘመኑ ተፈጽሞአል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ! በወንጌልም እመኑ!” ይል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጊዜው ደርሷል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ!” እያለ ይሰብክ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጊዜው ደርሶአል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ” እያለ ይሰብክ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዘመኑ ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ፤” እያለ ወደ ገሊላ መጣ። |
በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይፈርስና ግዛቱም በሌላ ሕዝብ የማይደፈር መንግሥትን ይመሠርታል፤ ይህ መንግሥት ሌሎችን መንግሥታት እስከ መጨረሻው ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤
ይህን ልብ ብለህ አስተውል፤ ኢየሩሳሌም እንድትታደስ ትእዛዝ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሳምንቶች ያልፋሉ፤ እንዲሁም ለሥልሳ ሁለት ሳምንት በችግር ጊዜ ኢየሩሳሌም፥ መንገዶችዋና የመከላከያ ጒድጓድዋ ይገነባሉ። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ የመከራ ዘመን ይሆናል።
‘እነሆ፥ በእግራችን ላይ ያለውን የከተማችሁን ትቢያ እንኳ እናራግፍላችኋለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ ቀረበች ዕወቁ።’
አሁን ግን ይህ እውነት ተገልጦአል፤ በዘለዓለማዊው አምላክ ትእዛዝ ሁሉም አምነው እንዲታዘዙ በነቢያት መጻሕፍት አማካይነት ሕዝቦች ሁሉ እንዲያውቁት ተደርጓል።
ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር በሥራ ላይ የሚያውለው ዕቅድ በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረቶች ሁሉ ተጠቃለው በአንዱ በክርስቶስ ሥልጣን ሥር እንዲሆኑ ነው።
ሰዎችን ሁሉ ከኃጢአት ለመዋጀት ራሱን ቤዛ አድርጎ የሰጠ እርሱ ነው፤ ይህም ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ የሚያስረዳ ምስክርነት ነው።