ነገር ግን በእውነት ለድኾች ይፈርዳል፤ ረዳት ለሌላቸውም ወገኖች ተከላካይ በመሆን መብታቸውን ያስከብራል፤ በበትር እንደሚመታ፥ መረን በተለቀቁት ላይ ይፈርዳል፤ በቃሉም ክፉዎችን ያጠፋል።
ሚልክያስ 4:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ መጥቼ ምድሪቱን እንዳልረግም እርሱ የወላጆችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ ወላጆች ይመልሳል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጥቼ ምድርን በርግማን እንዳላጠፋ፣ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጥቼ ምድርን በእርግማን እንዳልመታ፥ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመልሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል። |
ነገር ግን በእውነት ለድኾች ይፈርዳል፤ ረዳት ለሌላቸውም ወገኖች ተከላካይ በመሆን መብታቸውን ያስከብራል፤ በበትር እንደሚመታ፥ መረን በተለቀቁት ላይ ይፈርዳል፤ በቃሉም ክፉዎችን ያጠፋል።
ስለዚህም ርግማን ምድርን ያጠፋል፤ ሕዝቦችዋም በበደሉት በደል ተጠያቂዎች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይደመሰሳሉ፤ የሚተርፉትም ጥቂቶች ናቸው።
እኔ ጌታ እግዚአብሔርም እናንተን ለሞት አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የእናንተም ስም በእኔ ተመራጮች ዘንድ መራገሚያ ይሆናል፤ ለአገልጋዮቼ ግን የተለየ ስም እሰጣቸዋለሁ።
እስራኤላውያን ሁሉ ሕግህን ተላለፉ፤ የተናገርከውን ሁሉ ማዳመጥ እምቢ አሉ፤ አንተን ስለ በደልን በአገልጋይህ በሙሴ በኩል የተሰጠውን ሕግ በመሐላ የተገለጠውን ርግማን ሁሉ በእኛ ላይ አመጣህብን።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔም ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖር ለማንም ሰው ርኅራኄ አላደርግም፤ እኔ ራሴ እያንዳንዱን ሰው ለጐረቤቱና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያጠፋሉ፤ እኔም ከእነርሱ እጅ አልታደጋቸውም።”
ኢየሩሳሌምን ለመውጋት በሚነሣሡ ሕዝቦች ላይ እግዚአብሔር ቀሣፊ በሽታ ያመጣባቸዋል፤ በሕይወት እያሉ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዐይናቸው በዐይነስባቸው ውስጥ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ እግዚአብሔር ሕዝቦችን ሰብስቦ ይመጣል፤ ከተማይቱ ትያዛለች፤ ቤቶች ይበዘበዛሉ፤ ሴቶች ይደፈራሉ፤ ከሕዝቡም እኩሌታው ተማርኮ ይሄዳል፤ የቀሩት ግን ከከተማይቱ አይወጡም።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የተጠቀለለው መጽሐፍ በውስጡ በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚመጣው ርግማን ተጽፎበታል፤ የተጠቀለለው መጽሐፍ በአንድ በኩል ‘ሌባ ሁሉ ከምድር ይወገዳል’ የሚል ሲሆን፥ በሌላ በኩል ‘በመሐላ ሐሰት የሚናገር ሁሉ ይጠፋል’ ይላል።
ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ በብረት በትርም ይገዛቸዋል፤ እርሱ ሁሉን የሚችለውን የእግዚአብሔር አስፈሪ ቊጣ መግለጫ የሆነውን የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል፤