ሉቃስ 9:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት እላችኋለሁ፤ አሁን እዚህ ካሉት መካከል የእግዚአብሔር መንግሥት ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ የማይሞቱ አንዳንዶች አሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መካከል የእግዚአብሔርን መንግሥት ሳያዩ ሞትን የማይቀምሱ ሰዎች አሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነት እላችኋለሁ፤ በዚህ ከቆሙት አንዳንዶች የእግዚአብሔርን መንግሥት እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነት እላችኋለሁ፤ በዚህ ከቆሙት የእግዚአብሔርን መንግሥት እስኪያዩአት ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከሚቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ። |
ቀጥሎም ኢየሱስ፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ አሁን እዚህ ካሉት መካከል አንዳንዶች የእግዚአብሔር መንግሥት በታላቅ ኀይል ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ የማይሞቱ አሉ፤” አላቸው።
እኔ ግን እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፤ እኔ ካልሄድኩ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ከሄድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።
አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል።