ሉቃስ 7:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሴትዮዋ መለስ ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ስገባ አንተ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብክልኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን በእንባዋ አጥባ በጠጒርዋ አበሰችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፤ “ይህችን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ አንተ ለእግሮቼ ውሃ እንኳ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን እግሮቼን በእንባዋ እያራሰች በጠጕሯ አበሰች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጉርዋም አበሰች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፥ “ይህቺን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእግሮች ውኃ ስንኳ አልሰጠኸኝም፤ እርስዋ ግን አልቅሳ በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጕርዋም አበሰች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች። |
“ጌቶቼ ሆይ፥ ተቀብዬ ላስተናግዳችሁ ዝግጁ ነኝ፤ እባካችሁ ወደ ቤቴ ግቡ፤ እግራችሁንም ታጥባችሁ እዚሁ ዕደሩ፤ ጠዋት በማለዳ ተነሥታችሁ ጒዞአችሁን ትቀጥላላችሁ” አላቸው። እነርሱ ግን “አይሆንም፤ እኛ እዚሁ በከተማይቱ አደባባይ እናድራለን” አሉት።
ከዚህም በኋላ ዳዊት ኦርዮን “እንግዲህ ወደ ቤትህ ሂድና እግርህን ታጠብ” አለው፤ ኦርዮም ከዳዊት ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ዳዊትም ወዲያውኑ የምግብ ስጦታ ላከለት፤
ከኢየሱስ በስተኋላ በእግሮቹ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች እግሮቹን በእንባዋ ታርስና በጠጒርዋ ታብስ ነበር፤ እግሮቹን እየሳመች ሽቶ ትቀባቸው ነበር።
እንዲሁም ልጆችን በሚገባ በማሳደግ፥ እንግዳን በመቀበል፥ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፥ የተቸገሩትን በመርዳትና ማንኛውንም በጎ ሥራ ሁሉ በማከናወን ለመልካም ሥራም ሁሉ የተጋች መሆን አለባት።