ሉቃስ 7:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ወደ ኢየሱስ ሄደው፥ “ይህን ልታደርግለት የሚገባው ሰው ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልእክተኞቹም ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ እንዲህ ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ “ይህን ልታደርግለት ይገባዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ወደ ኢየሱስ መጥተው እንዲህ እያሉ አጥብቀው ለመኑት፦ “ይህን ልታደርግለት ይገባዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስም መጥተው ማለዱት፤ እንዲህም አሉት፥ “ፈጥነህ ውረድ፤ ይህን ልታደርግለት ይገባዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ወደ ኢየሱስ መጥተው፦ ይህን ልታደርግለት ይገባዋል፤ |
የመቶ አለቃው ስለ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ የአይሁድ ሽማግሌዎችን “እባካችሁ ኢየሱስ መጥቶ አገልጋዬን እንዲፈውስልኝ ሄዳችሁ ለምኑልኝ፥” ሲል ላካቸው።
እርሱ ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ሰው ነበረ፤ ለድኾችም ብዙ ምጽዋት ይሰጥ ነበር፤ ወደ እግዚአብሔርም ዘወትር ይጸልይ ነበር።
ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ እነርሱ ነጭ ልብስ መልበስ የሚገባቸው ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።