ሉቃስ 7:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአደባባይ ተቀምጠው የሚጫወቱ ልጆችን ይመስላል፤ እነርሱም እርስ በእርሳቸው እየተጠራሩ ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ እናንተ ግን አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ እናንተ ግን አላለቀሳችሁም፥’ የሚሉ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገበያ ቦታ ተቀምጠው እርስ በርሳቸው እየተጠራሩ እንዲህ የሚባባሉ ልጆችን ይመስላሉ፤ “ ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ አላለቀሳችሁም።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፤ እርስ በርሳቸውም እየተጠራሩ እንዲህ የሚሉትን እንቢልታ ነፋንላችሁ፤ አላሸበሸባችሁምም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ አላለቀሳችሁምም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገበያ ተቀምጠው ባልንጀሮቻቸውን ጠርተው፥ “አቀነቀንላችሁ፥ አልዘፈናችሁምም፤ ሙሾም አወጣንላችሁ፥ አላለቀሳችሁምም የሚሉአቸው ልጆችን ይመስላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እርስ በርሳቸውም እየተጠራሩ፦ እንቢልታ ነፋንላችሁ አልዘፈናችሁምም፤ ሙሾ አወጣንላችሁ አላለቀሳችሁምም ይላል። |