እነርሱ፥ ‘እኛ ቅዱሳን ስለ ሆንን ወደ እኛ አትቅረቡ!’ የሚሉ ናቸው፤ እነዚህ ነገሮች ቀኑን ሙሉ ለሚነድ እሳት ኀይለኛ ቊጣዬን የሚያቀጣጥሉ ናቸው።
ሉቃስ 6:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእኔ በሰው ልጅ ምክንያት ሰዎች ሲጠሉአችሁ፥ ሲለዩአችሁ፥ ሲያንቋሽሹአችሁና ስማችሁን ሲያጠፉ የተባረካችሁ ናችሁ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሏችሁ፣ ከመካከላቸው ሲለዩአችሁና ሲነቅፏችሁ፣ ክፉ ስምም ሲሰጧችሁ ብፁዓን ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ፥ ሲለዩአችሁና ሲነቅፉአችሁ፥ በክፉም ስማችሁን ሲያጠፉ ብፁዓን ናችሁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ቢጠሉአችሁ፥ ከሰው ለይተው ቢአሳድዱአችሁ፥ ቢሰድቡአችሁ፥ ክፉ ስምም ቢአወጡላችሁ ብፁዓን ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። |
እነርሱ፥ ‘እኛ ቅዱሳን ስለ ሆንን ወደ እኛ አትቅረቡ!’ የሚሉ ናቸው፤ እነዚህ ነገሮች ቀኑን ሙሉ ለሚነድ እሳት ኀይለኛ ቊጣዬን የሚያቀጣጥሉ ናቸው።
ቃሉን የምታከብሩ እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ “ስለ ስሜ የሚጠሉአችሁና የሚያገሉአችሁ እንዲህ ይሉአችኋል፦ ‘እናንተ ስትደሰቱ እናይ ዘንድ እስቲ እግዚአብሔር ክብሩን ይግለጥ፤’ ኀፍረት ላይ የሚወድቁት ግን እነርሱ ራሳቸው ናቸው።
ስለዚህ ልጁን ከወይኑ ተክል ቦታ ወደ ውጪ አውጥተው ገደሉት። ታዲያ፥ እንግዲህ የወይኑ ተክል ጌታ በእነዚህ ገበሬዎች ላይ ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል?
ሆኖም ከአይሁድ አለቆች እንኳ ብዙዎቹ በኢየሱስ አምነዋል፤ ነገር ግን ፈሪሳውያን ከምኲራብ እንዳያስወጡአቸው በመፍራት፥ በግልጥ አልመሰከሩለትም።
እስከዚህ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ የጳውሎስን ንግግር ያዳምጡ ነበር፤ ከዚህ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦ “እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከምድር ላይ ይወገድ! እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት መኖር አይገባውም!” እያሉ ጮኹ።