La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም በኋላ ዲያብሎስ ኢየሱስን ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው፤ በቤተ መቅደሱም ጣራ ጫፍ ላይ እንዲቆም አድርጎ፥ እንዲህ አለው፦ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ፥ እስቲ ከዚህ ወደታች ዘለህ ውረድ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ ከቤተ መቅደሱም ዐናት ላይ አውጥቶ፤ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ራስህን ወደ መሬት ወርውር፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ኢየሩሳሌም ደግሞ ወሰደው፤ በመቅደስም ጫፍ ላይ አቆመው፥ እንዲህም አለው፦ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ፥ ከዚህ ወደ ታች ራስህን ወርውር፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወስዶ በቤተ መቅ​ደሱ የማ​ዕ​ዘን ጫፍ ላይ አቆ​መው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ከሆ​ን​ህስ አንተ ራስህ ወደ ታች መር ብለህ ውረድ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ኢየሩሳሌም ደግሞ ወሰደው፤ በመቅደስም ጫፍ ላይ አቁሞ፦ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፥ እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ከዚህ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።

Ver Capítulo



ሉቃስ 4:9
7 Referencias Cruzadas  

በመግቢያው በር ያለው በረንዳም ቁመቱ ኀምሳ አራት ሜትር ሲሆን፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ወርድ ዘጠኝ ሜትር ነው፤ ውስጡም በንጹሕ ወርቅ እንዲለበጥ አደረገ።


እግዚአብሔርም ሰይጣንን “መልካም ነው፤ አትግደለው እንጂ በእርሱ ላይ የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ” አለው።


እነርሱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ፥ አንተ ከእኛ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን መጣህን?” እያሉ ጮኹ።


‘አንተን እንዲጠብቁህ እግዚአብሔር መላእክቱን ያዛል፤


ዲያብሎስም ኢየሱስን፦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እስቲ ይህን ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዝ” አለው።


እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድስናው መንፈስ ከሞት በመነሣቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በታላቅ ኀይል ታወቀ።