Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በመግቢያው በር ያለው በረንዳም ቁመቱ ኀምሳ አራት ሜትር ሲሆን፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ወርድ ዘጠኝ ሜትር ነው፤ ውስጡም በንጹሕ ወርቅ እንዲለበጥ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በቤተ መቅደሱ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ርዝመቱ በቤተ መቅደሱ ወርድ ልክ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ከፍታውም ሃያ ክንድ ነበር። ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሀያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በቤ​ቱም ፊት የነ​በ​ረው ወለል ርዝ​መቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስ​ጡ​ንም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 3:4
6 Referencias Cruzadas  

ብዙ ተአምራትና ድንቅ ነገሮች በሕዝቡ መካከል በሐዋርያት እጅ ይደረጉ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን መመላለሻ ይሰበሰቡ ነበር።


የዳነው ሰው ከጴጥሮስና ከዮሐንስ አልለይም በማለት ይዞአቸው ሳለ ሰዎቹ ተደንቀው “የሰሎሞን መመላለሻ” ወደሚባለው ስፍራ ወደ እነርሱ ሮጠው ሄዱ፤


ኢየሱስ በቤተ መቅደስ በሰሎሞን መተላለፊያ ይመላለስ ነበር።


በመግቢያው በር የሚገኘው በረንዳ ቁመቱ አራት ሜትር ተኩል፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ዘጠኝ ሜትር ነበር።


ከዚያ በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ ክፍል አመጣኝ፤ የመግቢያው ክፍል የግድግዳውም ዐምዶች ሲለካ የሁለቱም ትይዩ አምስት ክንድ ሆኖ አገኘው፤ የመግቢያውም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበር፤ የመግቢያውም ግድግዳ ውፍረት በሁለቱም በኩል ሦስት ሦስት ክንድ ነበር።


የማንጻቱ ሥራ በመጀመሪያው ወር መባቻ ቀን ተጀምሮ በስምንተኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ የሚያስገባው ክፍል ጭምር ሙሉ በሙሉ ተፈጸመ፤ ከዚህ በኋላም ቤተ መቅደሱን ለአምልኮ ሥነ ሥርዓት ለማዘጋጀት በተከታዮቹ ስምንት ቀኖች ማለትም ወሩ በገባ እስከ ዐሥራ ስድስተኛው ቀን ድረስ ሠሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios