ሉቃስ 23:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን እዚያ ቆመው በብርቱ ይከሱት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም እዚያው ቆመው በብርቱ ይወነጅሉት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህናት አለቆችና ጻፎችም በብርቱ እየከሰሱት ቆመው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህናት አለቆችና ጻፎችም ቆመው በብዙ ያሳጡት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናት አለቆችና ጻፎችም አጽንተው ሲከሱት ቆመው ነበር። |
እንዲህ እያሉም ይከሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት አገኘነው፤ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር እንዳይከፈል ይከለክላል፤ ደግሞ ‘እኔ ንጉሥ መሲሕ ነኝ’ እያለ ይናገራል።”