ሉቃስ 20:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ወዲህ ለኢየሱስ ጥያቄ ሊያቀርብለት የደፈረ ማንም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ አንድ ሰው እንኳ ሊጠይቀው አልደፈረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወዲህ ምንም ሊጠይቁት አልደፈሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያ ወዲህ ግን ሊጠይቀው የደፈረ ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ፊትም አንድ ነገር ስንኳ ሊጠይቁት አልደፈሩም። |
ኢየሱስም የሕግ መምህሩ በጥበብና በማስተዋል እንደ መለሰ አይቶ፥ “አንተስ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም፤” አለው። ከዚህ በኋላ ለኢየሱስ ጥያቄ ሊያቀርብለት የደፈረ ማንም የለም።