በግዛቱም ዘመን ሁሉ በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፥ የሊባኖስ ዛፍ ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅለው ሾላ ይቈጠር ነበር፤
ሉቃስ 19:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለ ነበር ዘኬዎስ እርሱን ለማየት ብሎ ከሕዝቡ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ በዚያ መንገድ ያልፍ ስለ ነበርም፣ ሊያየው ወደ ፊት ሮጦ አንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም መንገድ ማለፍ ነበረበትና ወደ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ላይ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ፊቱም ሮጠ፤ ያየው ዘንድም በሾላ ላይ ወጣ፤ በዚያች መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያችም መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ ወጣ። |
በግዛቱም ዘመን ሁሉ በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፥ የሊባኖስ ዛፍ ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅለው ሾላ ይቈጠር ነበር፤
በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በኢየሩሳሌም ወርቅና ብር ከመብዛቱ የተነሣ እንደ ድንጋይ ተራ ነገር ነበር፤ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅል ሾላ ዛፍ ይቈጠር ነበር።
በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፥ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅል ሾላ ይቈጠር ነበር።
“ከጡብ የተሠሩ ግንቦች ፈርሰዋል፤ እኛ ግን እንደገና በጥርብ ድንጋይ እንገነባቸዋለን፤ ከሾላ ግንድ የተሠሩ ምሰሶዎች ተሰብረዋል፤ እኛ ግን በምርጥ የሊባኖስ ዛፍ እንተካቸዋለን።”
ጌታ ኢየሱስም “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ በባሕር ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዝላችኋል” አላቸው።
ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ ቀና ብሎ ተመለከተና ዘኬዎስን፥ “ዘኬዎስ ሆይ! ዛሬ በአንተ ቤት መዋል ይገባኛልና ፈጥነህ ከዛፉ ውረድ” አለው።
ነገር ግን ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሽባውን ወደ ቤት ማግባት አቃታቸው፤ ስለዚህ ወደ ጣራ ላይ ይዘውት ወጡ፤ ጣራውንም ከፍተው በመካከሉ አውርደው ሽባውን ከነአልጋው በኢየሱስ ፊት አኖሩት።