ሉቃስ 19:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታውም ይህኛውን ‘አንተንም ደግሞ በአምስት ከተሞች ላይ ሾሜሃለሁ’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታውም፣ ‘አንተ ደግሞ በዐምስት ከተሞች ላይ ሥልጣን ተሰጥቶሃል’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህናውንም ‘አንተንም በአምስት ከተማዎች ላይ ሾሜሃለው፤’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱንም፦ አንተም በአምስት ከተሞች ተሾም አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ደግሞ፦ አንተም በአምስት ከተማዎች ላይ ሁን አለው። |
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።