ከዚህ በኋላ “አንድነት” የተባለውን ሁለተኛውን በትር ሰበርኩት፤ ይህንንም ማድረጌ በይሁዳና በእስራኤል መካከል የነበረው ወንድማማችነት መጥፋቱን ለማመልከት ነበር።
ሉቃስ 12:51 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በምድር ላይ ሰላምን ያመጣሁ ይመስላችኋልን? እኔስ ያመጣሁት መለያየትን እንጂ ሰላምን አይደለም እላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ ይመስላችኋል? አይደለም፤ እላችኋለሁ፤ እኔ የመጣሁት ለመለያየት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ላይ ሰላምንም ለመስጠት የመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፤ አይደለም፥ መለያየትን እንጂ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡንም እንዲህ አላቸው፥ “ለምድር ሰላምን ያመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፤ አይደለም፤ ሰይፍንና መለያየትን ነው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ ሰላምንም ለመስጠት የመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፥ አይደለም፥ መለያየትን እንጂ። |
ከዚህ በኋላ “አንድነት” የተባለውን ሁለተኛውን በትር ሰበርኩት፤ ይህንንም ማድረጌ በይሁዳና በእስራኤል መካከል የነበረው ወንድማማችነት መጥፋቱን ለማመልከት ነበር።