Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሉቃስ 12:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እነሆ! እኔ በምድር ላይ እሳት አምጥቻለሁ፤ ታዲያ፥ ቶሎ ቢቀጣጠልልኝ እንዴት በወደድኩ ነበር!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 “እኔ የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኰስ ነው፤ አሁኑኑ ቢቀጣጠል ምንኛ ደስ ባለኝ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 “በምድር ላይ እሳትን ልጥል መጣሁ፤ አሁን ቢቀጣጠል ምንኛ በወደድሁ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 “በም​ድር ላይ እሳ​ትን አም​ጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ን​ደድ በቀር ምን እሻ​ለሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ?

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 12:49
14 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን በእውነት ለድኾች ይፈርዳል፤ ረዳት ለሌላቸውም ወገኖች ተከላካይ በመሆን መብታቸውን ያስከብራል፤ በበትር እንደሚመታ፥ መረን በተለቀቁት ላይ ይፈርዳል፤ በቃሉም ክፉዎችን ያጠፋል።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።


ነገር ግን የጌታውን ፈቃድ ባለማወቅ፥ ቅጣት የሚያመጣበትን ነገር አድርጎ ቢገኝ ቅጣቱ ይቀልለታል፤ ብዙ ከተሰጠው ሰው ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ ዐደራም ከተሰጠው ሰው፥ ብዙ ይጠበቅበታል።”


ነገር ግን እኔ የምጠመቀው የመከራ ጥምቀት አለኝ፤ እርሱም እስኪፈጸም ድረስ ዕረፍት የለኝም።


ቀን ሆኖ ሳለ የላከኝን ሥራ መሥራት አለብኝ፤ ማንም ሰው ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት ይመጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos