Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 12:52 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 ከአሁን ጀምሮ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ አምስት ሰዎች ይለያያሉ፤ ሦስቱ በሁለቱ ላይ፥ ሁለቱም በሦስቱ ላይ ተነሥተው ይጣላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ከአሁን ጀምሮ እርስ በርስ የተለያዩ በአንድ ቤተ ሰብ ውስጥ ዐምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሁለቱ በሦስቱ ላይ፣ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 ከአሁን ጀምሮ በአንዲት ቤት አምስት ሰዎች ይኖራሉና፤ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ሁለቱም በሦስቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ አም​ስት ሰዎች በአ​ንድ ቤት ቢኖሩ ሦስቱ ከሁ​ለቱ፥ ሁለ​ቱም ከሦ​ስቱ ይለ​ያሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 ከአሁን ጀምሮ በአንዲት ቤት አምስት ሰዎች ይኖራሉና፤ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ሁለቱም በሦስቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 12:52
12 Referencias Cruzadas  

አንዳንዶቹ የተናገረውን ቃል አመኑ፤ ሌሎች ግን አላመኑም።


ከምኲራቦች አስወጥተው ያባርሩአችኋል፤ እንዲያውም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።


በዚህ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፥ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን “ታዲያ፥ ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እነዚህን ተአምራት እንዴት ማድረግ ይችላል?” አሉ። በዚህ ምክንያት በመካከላቸው መለያየት ሆነ።


እንጀራዬን ከእኔ ጋር አብሮ የበላ ከልብ የምተማመንበት ወዳጄ እንኳ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶአል።


እኔ በምድር ላይ ሰላምን ያመጣሁ ይመስላችኋልን? እኔስ ያመጣሁት መለያየትን እንጂ ሰላምን አይደለም እላችኋለሁ።


አባት በልጁ ላይ፥ ልጅም በአባቱ ላይ፥ እናት በሴት ልጅዋ ላይ፥ ሴት ልጅም በእናትዋ ላይ፥ ዐማት በምራትዋ ላይ፥ ምራትም በዐማትዋ ላይ በመነሣት ይለያያሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios