የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤ ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤ በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።
ሉቃስ 12:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ ከእናንተ መካከል በመጨነቅ በዕድሜው ላይ አንድ ቀን መጨመር የሚችል ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ፣ ከእናንተ ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ሰዓት መጨመር የሚችል ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተስ ዐስቦ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚቻለው ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? |
የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤ ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤ በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።