ሉቃስ 10:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰላም ወዳድ ሰው በዚያ ቤት ቢኖር ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለበለዚያ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰላም ሰው በዚያ ካለ፣ ሰላማችሁ ያርፍበታል፤ አለዚያም ሰላማችሁ ለእናንተው ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ በእርሱ ላይ ያድርበታል፤ ካልሆነ ግን ይመለስላችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር ሰላማችሁ ያድርበታል፤ ያለዚያ ግን ሰላማችሁ ይመለስላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያም ይመለስላችኋል። |
እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።
እባክሽን ይህን ጉዳይ አስቢበትና ማድረግ ስለሚገባሽ ነገር ወስኚ፤ አለበለዚያ ለጌታችንና ለቤተሰቡ ሁሉ አደገኛ ጥፋት ይሆናል፤ እርሱ እንደ ሆነ የማንንም ምክር የማይሰማ ደረቅ ሰው ነው!”