ሉቃስ 10:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በገባችሁበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ ‘ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን፥’ በሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወደ ማንኛውም ሰው ቤት ስትገቡ አስቀድማችሁ፣ ‘ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን’ በሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደምትገቡበትም ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ፦ ‘ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን፤’ በሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ገባችሁበት ቤትም አስቀድማችሁ ‘ለዚህ ቤት ሰዎች ሰላም ይሁን’ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ፦ ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ። |
ለመንገዳችሁ ምንም አትያዙ፤ የገንዘብ ቦርሳም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ ጫማም ቢሆን አትያዙ፤ ከሰው ጋር ሰላምታ በመለዋወጥ በመንገድ ላይ ቆማችሁ ጊዜ አታጥፉ።
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።
ለናባልም ይነግሩት ዘንድ እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጣቸው፦ “ሰላም ላንተ፥ ሰላም ለቤትህ፥ ሰላም ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን ብላችሁ ሰላምታ አቅርቡለት።