“በስምንተኛውም ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና አንድ ዓመት የሆናት አንዲት ቄብ ያምጣ፤ ከዚህም ጋር በወይራ ዘይት የተለወሰ ሦስት ኪሎ ግራም ዱቄትና የሊትር አንድ ሦስተኛ የሆነ የወይራ ዘይት ያምጣ።
ዘሌዋውያን 9:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባት ቀን የቈየው የክህነት አሰጣጥ ሹመት በተፈጸመ ማግስት ሙሴ አሮንንና ልጆቹን፥ እንዲሁም የእስራኤልን መሪዎች ጠራ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስምንተኛውም ቀን ሙሴ አሮንንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ። |
“በስምንተኛውም ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና አንድ ዓመት የሆናት አንዲት ቄብ ያምጣ፤ ከዚህም ጋር በወይራ ዘይት የተለወሰ ሦስት ኪሎ ግራም ዱቄትና የሊትር አንድ ሦስተኛ የሆነ የወይራ ዘይት ያምጣ።
የክህነት ሹመታችሁን ሥርዓት ለመፈጸም ሰባት ቀን ስለሚወስድ ይኸው ሥርዓት እስከሚፈጸምበት እስከ ሰባት ቀን ድረስ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትወጡም።