ዘሌዋውያን 8:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዘይቱም ጥቂት ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ በዚሁ ዐይነት ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለዩ ይሆኑ ዘንድ በመሠዊያውና ለእርሱ መገልገያ በተሠሩት ዕቃዎች ሁሉ ላይ እንዲሁም በመታጠቢያው ሳሕንና በሳሕኑ ማስቀመጫ ላይ ረጨ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዘይቱም ጥቂት ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውን ከነመገልገያ ዕቃው ሁሉ እንዲሁም የመታጠቢያ ሳሕኑን ከነማስቀመጫው በዘይት ቀባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ እንዲቀደሱም መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና መቀመጫውን ቀባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ፤ ድንኳኒቱንና ዕቃዋን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ። |
ስለ ኃጢአትም ይቅርታ በእያንዳንዱ ቀን አንድ ኰርማ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤ ይህም መሠዊያውን ያነጻል፤ የተቀደሰም ይሆን ዘንድ የወይራ ዘይት ቀባው።
ይህንንም ለሰባት ቀን በየዕለቱ አድርግ፤ በዚህም ዐይነት መሠዊያው ፍጹም የተቀደሰ ይሆናል፤ የተቀደሰም ስለ ሆነ፥ ሰውም ሆነ ሌላ ነገር እርሱን ቢነካ በቅድስናው ኀይል ቅሥፈት ይደርስበታል።
በዚህ ዐይነት እነዚህን ሁሉ በመለየት ፍጹም የተቀደሱ ታደርጋቸዋለህ፤ እነርሱንም ፍጹም ቅዱሳን ስለ ሆኑ ሰውም ሆነ ሌላ ነገር ቢነካቸው ቅሥፈት ይደርስበታል።
እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ብብትህ አስገባው” አለው፤ እርሱም እጁን ወደ ብብቱ አስገባ፤ እጁንም ከብብቱ ባወጣው ጊዜ እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”