“ለአሮን ክህነት ሥርዓት ከታረደው የበግ አውራ ፍርምባውን ወስደህ ለእኔ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ መባ አድርገህ አንሣ፤ ይህም ለእናንተው የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።
ዘሌዋውያን 7:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእስራኤላውያን የአንድነት መሥዋዕት መካከል የተወዘወዘውን ፍርንባና የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤላውያን እንደሚቀርብላቸው ቋሚ ድርሻ አድርጌ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች ወስጃለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ከእስራኤላውያን የሚያገኙት መደበኛ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚወዘወዘውን ፍርምባና እንደ ቁርባን የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕታቸው ወስጄ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ድርሻ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ እነርሱን ሰጥቼአቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚወዘወዘውን ፍርምባና የሚነሣውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘላለም እድል ፈንታ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ። |
“ለአሮን ክህነት ሥርዓት ከታረደው የበግ አውራ ፍርምባውን ወስደህ ለእኔ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ መባ አድርገህ አንሣ፤ ይህም ለእናንተው የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።
ለወገባቸውም መታጠቂያ አድርግላቸው፤ በራሳቸውም ላይ ቆብ ድፋላቸው፤ ክህነታቸው ለዘለዓለም ቋሚ ሥርዓት ይሆናል፤ በዚህም ዐይነት አሮንንና ልጆቹን ትሾማለህ።
ከእስራኤላውያን ወገን ስብ የሆነውን ሥጋ ወይም የእንስሶችን ደም የሚመገብ አይኑር፤ ይህም እስራኤላውያን በሚኖሩበት ዘመንና ቦታ ሁሉ ለዘለዓለሙ ተጠብቆ የሚኖር ቋሚ ሥርዓት ይሁን።
ከዚህም በኋላ ካህኑ ይህን ሁሉ ወስዶ ለእግዚአብሔር የሚወዘወዝ ልዩ መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ይህም ሁሉ የካህኑ ድርሻ ሆኖ ከሚነሣው ከአውራው በግ ፍርንባና ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት የሚፈቀድለትም ከዚያን በኋላ ነው።