“ስለ ኃጢአት ስርየት የቀረበውን መባ ስለምን በተቀደሰ ስፍራ አልበላችሁትም፤ እርሱ እጅግ የተቀደሰ ነው፤ እርሱንም የሕዝቡ ኃጢአት ማስወገጃ እንዲሆን እግዚአብሔር ለእናንተ ሰጥቶአችኋል፤
ዘሌዋውያን 6:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ |
“ስለ ኃጢአት ስርየት የቀረበውን መባ ስለምን በተቀደሰ ስፍራ አልበላችሁትም፤ እርሱ እጅግ የተቀደሰ ነው፤ እርሱንም የሕዝቡ ኃጢአት ማስወገጃ እንዲሆን እግዚአብሔር ለእናንተ ሰጥቶአችኋል፤
ጠቦቱንም ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕትና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ቅዱስ ስፍራ ያርደዋል፤ ይህንንም የሚያደርግበት ምክንያት የበደል ዕዳ መሥዋዕት ልክ ለኃጢአት ስርየት እንደሚቀርበው መሥዋዕት የካህኑ ድርሻ ሆኖ ስለሚሰጥ ነው፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።
“ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የኃጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርበው እንስሳ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ይታረድ። ይህም እጅግ የተቀደሰ ነው።