ዘሌዋውያን 27:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጹሕ ያልሆነ የእንስሳ በኲር ግን በይፋ በታወቀው ዋጋ ላይ በመቶ ኻያ እጅ ተጨምሮበት እንደገና መዋጀት ይችላል፤ ባለቤቱ የማይዋጀው ከሆነ ግን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሌላ ሰው ይሸጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንስሳው ርኩስ ከሆነ ግን፣ ባለቤቱ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ ዐምስተኛ ጨምሮ ሊዋጀው ይችላል፤ የማይዋጀው ከሆነ ግን በተተመነው ዋጋ ይሸጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የረከሰም እንስሳ ቢሆን እንደ ግምትህ መጠን ይቤዠዋል፤ በእርሱም ዋጋ ላይ አምስት እጅ ይጨምርበታል፤ ባይቤዥም እንደ ግምትህ ይሸጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የረከሰም እንስሳ ቢሆን እንደ ግምቱ ይቤዠው፤ በእርሱም የዋጋውን አምስተኛ እጅ ይጨምርበታል፤ ባይቤዥም እንደ ግምቱ ይሸጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የረከሰም እንስሳ ቢሆን እንደ ግምቱ ይቤዠው፥ በእርሱም የዋጋውን አምስተኛ ይጨምርበታል፤ ባይቤዥም እንደ ግምቱ ይሸጣል። |
“በኲር ሆኖ የሚወለድ እንስሳ ቀድሞውኑ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንም ሰው የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ ሊያቀርበው አይችልም፤ እንቦሳም ሆነ የበግና የፍየል ግልገሎች አስቀድመው ለእግዚአብሔር የተለዩ ናቸው፤
“አንድ ሰው የራሱን ሰውም ሆነ እንስሳን ወይም መሬትን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ እንዲሆን ካደረገው በኋላ ፈጽሞ ሊሸጠውም ሆነ መልሶ ሊዋጀው አይገባውም።
ቀድሞ መስጠት ይገባው ከነበረው ጋር አንድ አምስተኛ ጨምሮ ያምጣ፤ እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጥ፤ ካህኑም እንስሳውን ስለ ሰውየው ኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርበው፤ በደል የሠራውም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።