Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 27:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ከእርሱ ማንኛውንም ነገር መልሶ መዋጀት የሚፈልግ ሰው በይፋ በታወቀው ዋጋ ላይ በመቶ ኻያ እጅ ጨምሮ መግዛት ይችላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 አንድ ሰው ከዐሥራቱ የትኛውንም መዋጀት ቢፈልግ፣ በዋጋው ላይ አንድ ዐምስተኛ መጨመር አለበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ሰውም አሥራቱን ሊቤዥ ቢወድድ፥ በእርሱ ላይ አምስት እጅ ይጨምርበት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ሰውም ዐሥ​ራ​ቱን ሊቤዥ ቢወ​ድድ፥ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​መ​ር​በ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሰውም አሥራቱን ሊቤዥ ቢወድድ፥ አምስተኛ ይጨምርበታል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 27:31
5 Referencias Cruzadas  

ኢዮአስም ካህናቱን ጠርቶ በቤተ መቅደስ ከሚቀርበው መሥዋዕት ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ መባ ሆኖ የሚገባውን ገንዘብ ሁሉ በጥንቃቄ እንዲጠብቁ አዘዘ፤ ይኸውም ቋሚ ከሆነው ከዘወትር መሥዋዕት ጋር መባ ሆኖ የሚቀርበውንና በበጎ ፈቃድ ሕዝቡ የሚያመጣውን ስጦታ ሁሉ የሚያጠቃልል ነበር።


ንጹሕ ያልሆነ የእንስሳ በኲር ግን በይፋ በታወቀው ዋጋ ላይ በመቶ ኻያ እጅ ተጨምሮበት እንደገና መዋጀት ይችላል፤ ባለቤቱ የማይዋጀው ከሆነ ግን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሌላ ሰው ይሸጥ።


“ምድሪቱ የምታስገኘው እህልም ሆነ ፍራፍሬ ከዐሥር አንዱ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው።


ከቤት እንስሶች ከዐሥር አንዱ እጅ የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤ እንስሶች በሚቈጠሩበት ጊዜ ከዐሥር አንዱ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው።


ቀድሞ መስጠት ይገባው ከነበረው ጋር አንድ አምስተኛ ጨምሮ ያምጣ፤ እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጥ፤ ካህኑም እንስሳውን ስለ ሰውየው ኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርበው፤ በደል የሠራውም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos