ዘሌዋውያን 22:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ግን ንጹሕ ስለሚሆን የእርሱ ድርሻ የሆነውን የተቀደሰ የእህል መባ መብላት ይችላል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ የተቀደሰውን መሥዋዕት መብላት ይችላል፤ ምግቡ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ እንጀራው ነውና ከተቀደሰው ነገር ይበላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ምግቡ ነውና ከተቀደሰው ይብላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ እንጀራው ነውና ከተቀደሰው ይብላ። |
ለእኔ ከሚቀርበው እጅግ ከተቀደሰ መባ ሁሉ፥ ከእህል ቊርባን፥ ስለ ኃጢአት ስርየትና ስለ በደል ካሣ ከሚቀርበውም መባ ሁሉ፥ በእሳት የማይቃጠለው የመባ ድርሻ የአንተና የልጆችህ ነው።