ከዚህ በኋላ ያ ነቢይ ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘እኔ ይገደል’ ብዬ የፈረድኩበትን ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል፤ ”
ዘሌዋውያን 20:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሕዝቡ ያ ሰው ያደረገውን ሁሉ በቸልተኛነት ቢያልፈውና በሞት ባይቀጣው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአገሩ ሕዝብ፣ ሰውየው ልጁን ለሞሎክ ሲሰጥ አይተው ቸል ቢሉ፣ ባይገድሉትም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ልጁን ለሞሌክ ሲሰጥ፥ የአገሩ ሕዝብ አይቶ ያንን ሰው ፈጽሞ ቸል ቢለው ባይገድሉትም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘሩንም ለሞሎክ ሲሰጥ፥ የሀገሩ ሕዝብ ያን ሰው ቸል ቢሉት፥ አይተው እንዳላዩ ቢሆኑ፥ ባይገድሉትም፥ እኔ በዚያ ሰውና በቤተ ሰቡ ላይ ፊቴን አከብዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘሩንም ለሞሎክ ሲሰጥ፥ የአገሩ ሕዝብ ያን ቸል ቢለው ባይገድሉትም፥ |
ከዚህ በኋላ ያ ነቢይ ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘እኔ ይገደል’ ብዬ የፈረድኩበትን ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል፤ ”
ማንም ሰው ከልጆቹ አንዱን ለሞሌክ አሳልፎ በመስጠት የተቀደሰውን ድንኳኔን ቢያረክስና ቅዱስ ስሜንም ቢያሰድብ፥ ያ ሰው በእኔ ፊት የተጠላ ይሆናል፤ ከሕዝቡም ለይቼ አጠፋዋለሁ።
እኔ ራሴ በዚያ ሰውና በመላ ቤተሰቡ እንዲሁም ለእኔ ታማኝ ባለመሆን ለሞሌክ በመስገድ ከእርሱ ጋር በሚተባበሩት ሁሉ ላይ መዓቴን አመጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋቸዋለሁ።
እንግዲህ ሰዎች በቀድሞ ዘመን ባለማወቅ ያደረጉትን እግዚአብሔር ችላ ብሎ አልፎታል፤ አሁን ግን በየአገሩ ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡ አዞአል፤
ይሁን እንጂ እንደዚህ ያለውን ሰው ያግባባህ ዘንድ አትፍቀድለት፤ የሚናገረውን እንኳ አታድምጥ፤ ምሕረትም ሆነ ርኅራኄ በማድረግ ሕይወቱን ለማዳን አትሞክር።
እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን መቋቋም ያልቻሉበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እነርሱ ራሳቸው እንዲጠፉ ስለ ተፈረደባቸው ከጠላቶች ፊት ወደ ኋላ ይሸሻሉ። እንዲደመሰስ የታዘዘውን ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ እኔ ከእናንተ ጋር አልሆንም።
ነገር ግን የምነቅፍብህ አንዳንድ ነገሮች አሉኝ፤ ይኸውም የበለዓምን ትምህርት የያዙ አንዳንድ ሰዎች በመካከላችሁ አሉ፤ ይህ በለዓም የእስራኤል ሕዝብ ለጣዖት የተሠዋውን ምግብ በመብላትና ዝሙት በማድረግ እንዲሰናከሉ ባላቅን የመከረ ነው።