ለአምላካችሁ የምታቀርቡት የእህልም ሆነ የወይን ጠጅ መባ ስለሌለ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች የሆናችሁ ካህናት! ኑና ማቅ ለብሳችሁ ሌሊቱን ሁሉ አልቅሱ! እናንተም በመሠዊያው ላይ የምታገለግሉ ዋይ! ዋይ! በሉ።
ዘሌዋውያን 2:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእህሉንም መባ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ መሥዋዕት አድርገህ ለካህኑ ታስረክበዋለህ፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ሁኔታ የተዘጋጀውን የእህል ቍርባን ወደ እግዚአብሔር አምጥተህ ለካህኑ አስረክብ፤ ካህኑም ወደ መሠዊያው ይወስደዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእዚህም ነገረሮች የተዘጋጀውን የእህል ቁርባን ወደ ጌታ ታመጣለህ፤ ለካህኑም ይሰጣል፥ እርሱም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም ያደረግኸውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ታመጣለህ፤ ወደ ካህኑም ታቀርበዋለህ፤ ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም የተደረገውን የእህል ቍርባን ወደ እግዚአብሔር ታመጣለህ፤ ለካህኑም ይሰጣል፥ እርሱም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል። |
ለአምላካችሁ የምታቀርቡት የእህልም ሆነ የወይን ጠጅ መባ ስለሌለ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች የሆናችሁ ካህናት! ኑና ማቅ ለብሳችሁ ሌሊቱን ሁሉ አልቅሱ! እናንተም በመሠዊያው ላይ የምታገለግሉ ዋይ! ዋይ! በሉ።
ካህኑም ከዚያ መባ ከፊሉን ወስዶ በሙሉ ለእግዚአብሔር የቀረበ መሆኑን ለማስታወስ በመሠዊያው ላይ በሚገኘው እሳት ያቃጥለዋል፤ ይህም ዐይነት በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።