ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ለሚቀርበው ኅብስትና ዱቄት፥ ያለ እርሾ ለሚጋገረው ቂጣና በወይራ ዘይት ለሚለወሰው ዱቄት ኀላፊዎች ሲሆኑ፥ ለቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርበውን ሁሉ የሚመዝኑና የሚለኩ እነርሱ ነበሩ፤
ዘሌዋውያን 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መባው በመጥበሻ የተጋገረ ቂጣ ከሆነ የወይራ ዘይት ተጨምሮበት ከተለወሰ የላመ ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእህል ቍርባንህ በመጥበሻ የሚበስል ከሆነ፣ ከላመ ዱቄትና ከዘይት ይዘጋጅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁርባንህም በመጥበሻ የተጋገረ የእህል ቁርባን ቢሆን፥ ዘይት የገባበት ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍርባንህም በመቀቀያ የበሰለ ቍርባን ቢሆን፥ ዘይት የገባበት ከመልካም ስንዴ ዱቄት የተደረገ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍርባንህም በመቀቀያ የበሰለ የእህል ቍርባን ቢሆን፥ ዘይት የገባበት ከመልካም ዱቄት የተደረገ ይሁን። |
ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ለሚቀርበው ኅብስትና ዱቄት፥ ያለ እርሾ ለሚጋገረው ቂጣና በወይራ ዘይት ለሚለወሰው ዱቄት ኀላፊዎች ሲሆኑ፥ ለቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርበውን ሁሉ የሚመዝኑና የሚለኩ እነርሱ ነበሩ፤