ዘሌዋውያን 18:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናትና ከሴት ልጅዋ፥ እንዲሁም ከልጅ ልጆችዋ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ፤ እነርሱም የቅርብ ዘመዶችህ ስለ ሆኑ ኃጢአት ይሆንብሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከእናቲቱና ከሴት ልጇ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እነርሱ የሥጋ ዘመዶቿ ናቸው፤ ይህም ጸያፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴትንና የሴት ልጇን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጇን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጇን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ እርሷን አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ዝሙት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴትንና የሴት ልጅዋን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ኀጢአት ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴትንና የሴት ልጅዋን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ዝሙት ነው። |
አንድ ሰው እናትና ሴት ልጅዋን ቢያገባ፥ ስለ ፈጸሙት ክፉ ድርጊት ሦስቱም በእሳት ተቃጥለው ይገደሉ፤ እንዲህ ያለው ነገር በመካከላችሁ መፈጸም የለበትም።
ደካሞችንና ረዳት የሌላቸውን በትቢያ ላይ ጥለው ራስ ራሳቸውን ይረግጣሉ፤ የተዋረዱ ምስኪኖችንም ገፍትረው ከመንገድ ያስወጣሉ፤ አባትና ልጅ ሁለቱም ከአንዲት ሴት ጋር ያመነዝራሉ፤ በዚህም ሥራቸው የተቀደሰውን ስሜን ያረክሳሉ።