ዘሌዋውያን 16:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተመረጠውን ፍየል እየነዳ ወደ በረሓ ይዞት ሄዶ የነበረውም ሰው ወደ ሰፈር ከመግባቱ በፊት ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም ይታጠብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሚለቀቀውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ዐዛዜል የሄደውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመለቀቅ የሚሆነውን ፍየል የወሰደ ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመለቀቅ የሚሆነውን ፍየል የወሰደ ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል። |
በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ በእናንተ ዘንድ የረከሰ ይሆናል፤ የእርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ይሆናል፤
በድናቸው የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ይረክሳል፤ ይኸውም ከእንጨት የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ልብስን፥ ቆዳን ወይም ከረጢት የመሳሰሉትንና ሌላውንም ነገር ሁሉ ይጨምራል፤ የእነርሱ በድን የነካው ይህን የመሰለ ዕቃ ሁሉ በውሃ ውስጥ ተነክሮ ይቈይ፤ እስከ ምሽትም ድረስ ርኩስ ሆኖ ከዚያ በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
ማንም ከዚህ እንስሳ ማንኛውንም ክፍል ቢበላ ልብሱን ይጠብ፤ እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሁን፤ ማንም ሰው የዚያን እንስሳ በድን ቢሸከም ልብሱን ይጠብ፤ እርሱም እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሁን።
ከበሽታው የነጻው ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ጠጒሩን ሁሉ ይላጫል፤ ሰውነቱንም ይታጠባል፤ ከዚያም በኋላ የነጻ ሆኖ ወደ ሰፈር ይገባል፤ ነገር ግን እስከ ሰባት ቀን ከራሱ ድንኳን ውጪ መቈየት አለበት።
ይህን ሕግ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ ለማንጻት የሚያገለግለውን ውሃ በላዩ የሚረጨው ሰው ልብሱን ማጠብ ይኖርበታል፤ ውሃውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ያልነጻ ሆኖ ይቈያል፤