ዘሌዋውያን 15:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ከእነርሱ አንዱን ኃጢአት የሚሰረይበት መሥዋዕት፥ ሌላውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መሠረት ስለ ፈሳሹ በእግዚአብሔር ፊት ለሰውየው ያስተሰርይለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም በጌታ ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም አንዲቱን ለኀጢአት መሥዋዕት፥ አንዲቱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስተሰርይለታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል። |
በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ በእናንተ ዘንድ የረከሰ ይሆናል፤ የእርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ይሆናል፤
በድናቸው የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ይረክሳል፤ ይኸውም ከእንጨት የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ልብስን፥ ቆዳን ወይም ከረጢት የመሳሰሉትንና ሌላውንም ነገር ሁሉ ይጨምራል፤ የእነርሱ በድን የነካው ይህን የመሰለ ዕቃ ሁሉ በውሃ ውስጥ ተነክሮ ይቈይ፤ እስከ ምሽትም ድረስ ርኩስ ሆኖ ከዚያ በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
ማንም ከዚህ እንስሳ ማንኛውንም ክፍል ቢበላ ልብሱን ይጠብ፤ እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሁን፤ ማንም ሰው የዚያን እንስሳ በድን ቢሸከም ልብሱን ይጠብ፤ እርሱም እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሁን።
ካህኑም ስጦታዋን ተቀብሎ ለእግዚአብሔር ያቀርባል፤ የደም መፍሰስ ርኵሰትዋ ተወግዶ የምትነጻበትንም ሥርዓት ይፈጽማል፤ ከዚያም በኋላ የነጻች ትሆናለች፤ ይህም እንግዲህ ወንድ ወይም ሴት ከወለደች በኋላ የምትፈጽመው ሕግ ሆኖ ይኖራል።
“ሴትዮዋ የበግ ጠቦት ማምጣት ካልቻለች፥ ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ታምጣ፤ እነርሱም አንዱ ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ይቀርባሉ፤ ካህኑም ያስተሰርይላትና ትነጻለች፤ ከዚያም በኋላ የነጻች ትሆናለች።”
አፈጻጸሙም ለኃጢአት መሥዋዕት በሚቀርበው ኰርማ ላይ በሚደረገው ዐይነት ይሁን፤ በዚህም ዐይነት ስለ ሕዝቡ ኃጢአት መሥዋዕትን ያቀርባል፤ ሕዝቡም የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ።
ስቡንም ሁሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ የዚህም አፈጻጸም ለአንድነት መሥዋዕት የቀረቡትን እንስሶች ስብ ባቃጠለው ዐይነት ይሁን፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ ስለ ሕዝቡ መሪ ኃጢአት መሥዋዕት በማቅረብ ያስተሰርያል፤ መሪውም የኃጢአቱን ይቅርታ ያገኛል።
ለአንድነት መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶችን ስብ በመግፈፍ በሚፈጽመው ዐይነት የዚህችንም እንስሳ ስብ ሁሉ ገፎ ያስወግድ፤ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በዚህ ዐይነት ካህኑ ስለዚያ ሰው የኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ያቀርባል፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።
ከዚህም በኋላ ለአንድነት መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶችን ስብ በመግፈፍ በሚፈጽመው ዐይነት የዚህችንም እንስሳ ስብ ሁሉ ገፎ ያስወግድ፤ እርሱንም ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው የምግብ መባ ጋር በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ ስለዚያ ሰው የኃጢአት መሥዋዕትን በማቅረብ ያስተስርይለት፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።
ካህኑም ለመላው የእስራኤል ማኅበር ያስተስርይላቸው፤ ስሕተቱን የፈጸሙት ባለማወቅ ስለ ሆነና ስለ ኃጢአት ስርየት የሚሆነውንም መሥዋዕትና የእህል ቊርባን አድርገው ለእግዚአብሔር ስላቀረቡ፥ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል።
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ትክክል ነው። በኀያል ቃሉ ዓለምን ሁሉ ደግፎ ይዞአል፤ ሰዎችንም ከኃጢአት ካነጻ በኋላ በሰማይ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል።