ዘሌዋውያን 13:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድሩም ሆነ በማጉ ላይ፥ እንዲሁም ከሱፍ ወይም ከቈዳ ወይም ከቈዳ በተሠራ ልብስ ላይ ቢታይና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሸማኔ ዕቃ ወይም በእጅ የተሠራ ማንኛውም ዐይነት የበግ ጠጕር ወይም የበፍታ ልብስ ወይም ማንኛውም ቈዳ ወይም ከቈዳ የተሠራ ነገር ቢሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ በፍታ ወይም የበግ ጠጉር ቢሆን፥ በተለፋው ቆዳ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ ቢሆን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ የበግ ጠጕር ወይም የተልባ እግር ቢሆን፥ ቆዳ ወይም ከቆዳ የሚደረግ ነገር ቢሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ በፍታ ወይም የበግ ጠጕር ቢሆን፥ አጐዛ ወይም ከአጐዛ የሚደረግ ነገር ቢሆን፥ |
በሰባተኛውም ቀን እንደገና በሚመረምረው ጊዜ ሻጋታው ነገር ተስፋፍቶ ከታየበት ያ የታየው አጥፊ ሻጋታ ስለ ሆነ፥ የዚያ ዐይነቱ ልብስ ሁሉ ርኩስ ነው፤
አንዳንዶችን ከእሳት አውጥታችሁ አድኑአቸው፤ ለሌሎች በፍርሃት ራሩላቸው፤ ሆኖም በኃጢአት የረከሰውን ሰውነታቸውን የነካውን ልብስ እንኳ ሳይቀር ጥሉ።
ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ እነርሱ ነጭ ልብስ መልበስ የሚገባቸው ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።