ዘሌዋውያን 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽኮኮ ያመሰኳል፤ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽኮኮ ያመሰኳል፤ ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ግን በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽኮኮ ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥንቸል ያመሰኳል፤ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ይህ ለእናንተ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሽኮኮ ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። |
ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው የሚከተሉትን አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፤ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።
ነገር ግን ሰኮናቸው ያልተከፈለውንና የማያመሰኩትን እንስሶች አትብሉ፤ በዚህም ዐይነት ግመል፥ ጥንቸልና ሽኮኮ የመሳሰሉትን አትብሉ፤ እንደነዚህ ያሉት እንስሶች የሚያመሰኩ ቢሆኑም ሰኮናቸው ያልተከፈለ በመሆኑ የረከሱ ሆነው ይቈጠራሉ፤
“እግዚአብሔርን እናውቃለን” ይላሉ፤ በሥራቸው ግን ይክዱታል፤ እነርሱ አጸያፊዎች፥ የማይታዘዙና ምንም መልካም ሥራ ማድረግ የማይችሉ ናቸው።