ዘሌዋውያን 11:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰኮናው ስንጥቅ የሆነውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ትበላላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰኰናው የተሰነጠቀውን የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሁለት የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ሁሉ ብሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተሰነጠቀ ሰኰና ያለውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ሁሉ ብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ሁሉ ብሉ። |
ሰኰና ያለው፥ ነገር ግን ሰኰናው በሙሉ ያልተሰነጠቀና የማያመሰኩ እንስሳ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱን የሚነካ ሁሉ ይረክሳል፤
ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው የሚከተሉትን አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፤ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።
በቤርያ ያሉት አይሁድ በተሰሎንቄ ካሉት ይልቅ ቅን አመለካከት ያላቸው ስለ ነበሩ ቃሉን በታላቅ ደስታ ተቀበሉ፤ የቃሉንም እውነተኛነት ለማረጋገጥ በየቀኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይመረምሩ ነበር።
ዐሣማዎችን አትብሉ፤ እነርሱ ሰኮናቸው የተከፈለ ቢሆንም ስለማያመሰኩ የረከሱ ሆነው ይቈጠራሉ፤ እንደነዚህ ያሉትን እንስሶች መብላት ይቅርና በድናቸውን እንኳ አትንኩ።