እነሆ፥ ከሰማይ በታች ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት የጥፋት ውሃ አመጣለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ይጠፋል።
መሳፍንት 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ነገሥታት ስሙ! እናንተም አለቆች አድምጡ! እኔ ለእግዚአብሔር፥ እዘምራለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር አዜማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ ነገሥታት ይህን ስሙ፤ ገዦችም አድምጡ፤ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ደግሜም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገሥታት ሆይ፥ ስሙ፥ መኳንንት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔ ለጌታ እቀኛለሁ፥ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ እዘምራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሥታት ሆይ፥ ስሙ፤ ጽኑዓን መኳንንትም ሆይ፥ አድምጡ፤ እኔ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤ እኔ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሥታት ሆይ፥ ስሙ፥ መኳንንት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ። |
እነሆ፥ ከሰማይ በታች ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት የጥፋት ውሃ አመጣለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ይጠፋል።
ከዚህ በኋላ ኤልያስ እንዲህ አለ፦ “ከእግዚአብሔር ነቢያት የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያት ግን እነሆ በዚህ አሉ፤
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔን እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ” ሲል መለሰ።
“እኔ ንጉሥ አርጤክስስ ከኤፍራጥስ ምዕራብ የምትገኙ በጅሮንዶች ሁሉ በሰማይ አምላክ ሕግ ምሁር የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ ትሰጡት ዘንድ አዝዣለሁ።
አሁን ግን በከበቡኝ ጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ አደረግሁ፤ በደስታ “እልል” እያልኩ በመቅደሱ ውስጥ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ እየዘመርኩም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
ከእርሱም ጋር እንዲሠራ ከዳን ነገድ የአሒሳማክን ልጅ ኦሆሊአብን መርጬአለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን ነገር ሁሉ እንዲሠሩ ሌሎችም የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ታላቅ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጌአለሁ።