ስለዚህም ጠላቶቻቸው እነርሱን ድል አድርገው ይገዙአቸው ዘንድ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፤ እነርሱም አስጨነቁአቸው። በችግራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ አንተም በሰማይ ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከምሕረትህ ታላቅነት የተነሣ፥ ከጠላቶቻቸው የሚታደጉ መሪዎችን ላክህላቸው።
መሳፍንት 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብ ታናሽ ወንድም ልጅ የሆነውን የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን አስነሣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ ግን የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን ወደ ጌታ በጮኹ ጊዜ ግን፥ ጌታ የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔርም ለእስራኤል መድኀኒትን አስነሣላቸው። የካሌብ የታናሽ ወንድሙ የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያልም አዳናቸው፤ ለእርሱም ታዘዙለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብን የታናሽ ውንድሙን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አስነሣላቸው። |
ስለዚህም ጠላቶቻቸው እነርሱን ድል አድርገው ይገዙአቸው ዘንድ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፤ እነርሱም አስጨነቁአቸው። በችግራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ አንተም በሰማይ ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከምሕረትህ ታላቅነት የተነሣ፥ ከጠላቶቻቸው የሚታደጉ መሪዎችን ላክህላቸው።
ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን “አንተን አምላካችንን ትተን በዓል ተብለው የሚጠሩትን ባዕዳን አማልክት በመከተላችን በአንተ ላይ በደል ሠርተናል” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
እግዚአብሔር መስፍን ባስነሣላቸው ጊዜ ሁሉ እርሱ ከመስፍኑ ጋር ነበር፤ በሚያሳድዱአቸውና በሚጨቊኑአቸው ጠላቶች ምክንያት ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር በሚጮኹበት ጊዜ እግዚአብሔር ያዝንላቸው ስለ ነበረ በመስፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ ያድናቸው ነበር።
ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ ግራኝ የነበረውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሣቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞአብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት።
ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ፤ ለመስጴጦምያው ንጉሥ ለኩሻን ፊሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለኩሻን ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት ተገዙለት፤
ያቢን ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎች ነበሩት፤ የእስራኤል ሕዝብ በጭካኔና በዐመፅ ለኻያ ዓመት ገዛቸው፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
ከዚያም በኋላ እነርሱ ‘አንተን ትተን በዓልንና ዐስታሮትን በማምለካችን በድለናል፤ አሁንም ከጠላቶቻችን አድነን፤ እናመልክህማለን!’ ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።