መሳፍንት 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔርም ለእስራኤል መድኀኒትን አስነሣላቸው። የካሌብ የታናሽ ወንድሙ የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያልም አዳናቸው፤ ለእርሱም ታዘዙለት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ ግን የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እስራኤላውያን ወደ ጌታ በጮኹ ጊዜ ግን፥ ጌታ የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብ ታናሽ ወንድም ልጅ የሆነውን የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን አስነሣቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብን የታናሽ ውንድሙን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አስነሣላቸው። Ver Capítulo |