ሴዴቅያስ፥ ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር ስም ባስማለው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ተጸጽቶ ንስሓ በመግባት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በእልኸኛነት እምቢ አለ።
ኢያሱ 9:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእነርሱ የምናደርገው እንደዚህ ነው፦ ለእነርሱ ስለማልንላቸው መሐላ የእግዚአብሔር ቊጣ እንዳይደርስብን በሕይወት እንዲኖሩ እንተዋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ እናደርግላቸዋለን፤ የገባንላቸውን መሐላ በማፍረስ ቍጣ እንዳይደርስብን፣ በሕይወት እንዲኖሩ እንዲሁ እንተዋቸዋለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ማልንላቸው መሓላ ቁጣ እንዳይወርድብን ይህን እናድርግባቸው፥ በሕይወትም እንዲኖሩ እንተዋቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለማልንላቸው መሐላ ጥፋት እንዳይሆንብን ይህን አናድርግባቸው፤ በሕይወትም እንተዋቸው፤ እንግዛቸውም” አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ማልንላቸው መሓላ ቁጣ እንዳይወርድብን ይህን እናድርግባቸው፥ በሕይወትም እንተዋቸው አሉአቸው። |
ሴዴቅያስ፥ ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር ስም ባስማለው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ተጸጽቶ ንስሓ በመግባት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በእልኸኛነት እምቢ አለ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።
ለአመንዝሮችና ግብረ ሰዶምን ለሚያደርጉ፥ ሰውን አፍነው በመውሰድ ለሚሸጡ ነጋዴዎችና ለውሸታሞች፥ በሐሰት ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው፤
መሪዎቹ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ገብተንላቸዋል፤ ስለዚህም አሁን ጒዳት ልናደርስባቸው አይገባም፤