እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቈዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።
ኢያሱ 8:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህን ጊዜ እናንተ ከተደበቃችሁበት ስፍራ ወጥታችሁ ከተማይቱን ያዙ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔርም ከተማይቱን ለእናንተ አሳልፎ ይሰጣችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም ከተደበቃችሁበት ትወጡና ከተማዪቱን ትይዛላችሁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከተማዪቱን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፤ ጌታም አምላካችሁ እርሷን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማይቱን ያዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማዪቱን ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማይቱን ያዙ። |
እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቈዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “የጦር ወታደሮችህን ይዘህ ወደ ዐይ ከተማ ለመዝመት ውጣ፤ ከቶ አትፍራ፤ ደፋር ሁን፤ እኔ በዐይ ንጉሥ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አድርጌሃለሁ፤ ሕዝቡ፥ ከተማይቱና ምድሪቱ የአንተ ይሆናሉ፤
ከዚህም የተነሣ ዳዊት እንደገና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “እኔ በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን ስለማቀዳጅህ ሄደህ በቀዒላ ላይ አደጋ ጣል” አለው።