Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 8:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማይቱን ያዙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እናንተም ከተደበቃችሁበት ትወጡና ከተማዪቱን ትይዛላችሁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከተማዪቱን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፤ ጌታም አምላካችሁ እርሷን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማይቱን ያዙ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በዚህን ጊዜ እናንተ ከተደበቃችሁበት ስፍራ ወጥታችሁ ከተማይቱን ያዙ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔርም ከተማይቱን ለእናንተ አሳልፎ ይሰጣችኋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እን​ግ​ዲህ እና​ን​ተም ከተ​ደ​በ​ቃ​ች​ሁ​በት ስፍራ ተነሡ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ስ​ዋን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያዙ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 8:7
6 Referencias Cruzadas  

የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማን እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበረ፤ ደግሞም ጽኑዕ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ።


እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ አትፍራ፥ አትደንግጥ፥ ሰልፈኞችን ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ፥ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ፥ እይ፥ የጋይን ንጉሥ ሕዝቡንም ከተማውንም ምድሩንም በእጅህ ሰጥቼሃለሁ።


አስቀድመን እንደ ሸሸን የምንሸሽ ይመስላቸዋልና ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል፥ እኛም ከፊታቸው እንሸሻለን።


በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን በእሳት አቃጥሉአት፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል አድርጉ፥ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።


ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም መልሶ፦ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቅዒላ ውረድ አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos