ኢያሱ 5:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው ሁሉም እስኪያልቁ ድረስ እስራኤላውያን በበረሓ ለአርባ ዓመት ተጓዙ። ለልጅ ልጆቻቸው ሊሰጥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ቃል ገብቶ የነበረውን በማርና በወተት የበለጸገውን ምድር በምድረ በዳ ያለቁት ልጆቻቸው እንደማያዩት አረጋግጦ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብጽን ለቅቀው በወጡ ጊዜ መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ለእግዚአብሔር ስላልታዘዙ፣ እነርሱ ሞተው እስኪያልቁ ድረስ፣ እስራኤላውያን በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይንከራተቱ ነበር። እግዚአብሔር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው ቃል የገባላቸውን ያችን ማርና ወተት የምታፈስስ ምድር እንደማያዩአት ምሏልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ እንዲሰጠን ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ የጌታንም ቃል ያልሰሙ፥ ሕዝብ ሁሉ፥ ከግብጽ የወጡ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻችን የማለላቸውን ምድር እንደማያሳያቸው የማለባቸውን፥ ከግብፅ የወጡ የእግዚአብሔርንም ቃል ያልሰሙ፥ እነዚያ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በመድበራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ ከግብፅ የወጡ የእግዚአብሔርንም ቃል ያልሰሙ፥ እነዚያ ሰልፈኞች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር። |
በግፍ ጭቈና ከሚሠቃዩባት ከግብጽ ምድር አውጥቼ እነሆ ዛሬ፥ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገች ሰፊና ለም የሆነች ምድር ልሰጣቸው ቃል ገብቻለሁ።
እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ።
“ሂድና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በመጀመሪያ በምድረ በዳ ምንም በማያበቅልበት ትከተሉኝ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ ለሙሽራው የምታሳየውን ፍቅርና ታማኝነት ለኔም ታሳይ እንደ ነበረ አስታውሳለሁ።
ከዚህም በላይ ከዓለም ምድር ሁሉ ውብ የሆነችውንና በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እሰጣችኋለሁ ብዬ ቃል ገብቼላቸው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በበረሓ እያሉ ወደዚያ እንደማላስገባቸው አረጋግጬ ነገርኳቸው።
ከግብጽ ምድር አወጣኋቸው፤ ለእነርሱ የመረጥኩላቸው ምድር በማርና በወተት የበለጸገች ነበረች፤ እርስዋም ከዓለም ምድር ሁሉ ይበልጥ የተዋበች ነበረች፤ ወደዚያች ምድርም እንደማስገባቸው ቃል የገባሁላቸው በዚያን ጊዜ ነው።
“በዚያን ጊዜ ተራራዎችም ሁሉ በወይን ተክል ይሸፈናሉ፤ በኰረብቶችም ላይ ብዙ ወተት የሚሰጡ ከብቶች ይሰማራሉ፤ በይሁዳ ምድር የሚገኙ ወንዞች ሁሉ በውሃ የተሞሉ ይሆናሉ፤ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ምንጭ ይፈልቃል፤ የሺጢምንም ሸለቆ ያጠጣል።
ስለዚህ ለቀድሞ አባቶቻቸው ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር በፍጹም አይገቡም፤ እኔን ከናቁኝ ሰዎች መካከል አንድ እንኳ ወደዚያች ምድር ከቶ አይገባም።
ሙሴና አልዓዛር በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባለው በሞአብ ሜዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩበት ጊዜ የመዘገቡአቸው የጐሣ መሪዎች እነዚህ ነበሩ።
ግብጽን ለቀው ከወጡ በኋላ አርባኛው ዓመት በገባ በዐሥራ አንደኛው ወር መጀመሪያ ቀን ሙሴ ለሕዝቡ ያስረዳቸው ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው።
ይህም የሆነው ቃዴስ በርኔን ትተን ከሄድን ከሠላሳ ስምንት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው፤ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ አስቀድሞ በመሐላ በተናገረው መሠረት ለጦርነት የደረሱ የዚያ ትውልድ ወንዶች ሁሉ አልቀው ነበር።
“በእርግጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሠራችሁት ሥራ ሁሉ ብዙ በረከት ሰጥቶአችኋል፤ በዚህ በሰፊው በረሓ በሄዳችሁበት ሁሉ ተንከባክቦአችኋል፤ በእነዚህ በአርባ ዓመቶች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለ ነበረ ምንም የጐደለባችሁ ነገር አልነበረም።
እረዳቸው ዘንድ ወደ እኔ ጮኹ፤ እኔም በእነርሱና በግብጻውያን መካከል ጨለማ እንዲሆን አደረግሁ። ባሕሩም እንዲከነበልባቸው አድርጌ ግብጻውያንን አሰጠምሁ፤ በግብጻውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ በዐይኖቻችሁ አይታችኋል፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ለብዙ ጊዜ በበረሓ ኖራችሁ።