ኢያሱ 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቀድማችሁ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ውረዱ፤ በእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ ስም፥ እያንዳንዳችሁ አንዳንድ ድንጋይ በማንሣት በትከሻችሁ ተሸከሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አላቸው፤ “ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድማችሁ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዕለፉ፤ እያንዳንዳችሁም በእስራኤል ነገድ ቍጥር አንዳንድ ድንጋይ በትከሻችሁ ተሸከሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በጌታ ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል እለፉ፤ ከእናንተም ሰው ሁሉ በእስራኤል ልጆች ነገድ ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም አላቸው፥ “በእኔና በእግዚአብሔር ፊት ወደ ዮርዳኖስ መካከል ዕለፉ፤ እያንዳንዱ ሰው በዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም አላቸው፦ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ወደ ዮርዳኖስ መካከል እለፉ፥ ከእናንተም ሰው ሁሉ በእስራኤል ልጆች ነገድ ቁጥር በጫንቃው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም። |
ሙሴም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጻፈ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ በተራራው ሥር መሠዊያ ሠራ፤ ለእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንድ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤
የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራችሁ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ ታላላቅ የሆኑ ጥቂት ድንጋዮችን አቁመህ በኖራ ለስነው፤
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አድምጥ፤ ከአንተ የሚበልጡትንና በኀይልም ብርቱ የሆኑትን የአሕዛብ ምድርና ቅጽሮቻቸው እስከ ሰማይ የደረሱ ታላላቅ ከተሞቻቸውን ለመውረስ ትገባ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገራለህ።
የሮቤል፥ የጋድና የምሥራቅ ምናሴ ነገዶች በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በከነዓን ምድር ወደሚገኘው ወደ ገሊሎት እንደ ደረሱ በወንዙ አጠገብ አስደናቂ የሆነ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ፤
እነዚህም ድንጋዮች እግዚአብሔር ያደረገውን ነገር ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ የሚያስታውሱ መታሰቢያዎች ይሆናሉ፤ በሚመጡትም ዘመናት ልጆቻችሁ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድናቸው?’ ብለው በሚጠይቁአችሁ ጊዜ፥