እነርሱም በገለዓድ ምድር ብዙ የከብት መንጋ ስለ ነበራቸው በስተ ምሥራቅ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ተንጣልሎ ያለውን በረሓማ ምድር ሁሉ ያዙ።
ኢያሱ 22:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን በምርኮ ያገኛችሁትን ብዙ ከብት፥ ብር፥ ወርቅ፥ ነሐስ፥ ብረትና ብዙ ልብሶች ይዛችሁ ወደ መኖሪያችሁ ልትመልሱ ስለ ሆነ ከጠላቶቻችሁ በምርኮ ያገኛችሁትን ምርኮ ከዘመዶቻችሁ ጋር ተካፈሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አላቸው፤ “ብዙ ሀብት ይዛችሁ ማለትም አያሌ የከብት መንጋ፣ ብርና ወርቅ፣ ናስና ብረት እንዲሁም ቍጥሩ እጅግ የበዛ ልብስ ይዛችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ ከጠላት የተገኘውንም ይህን ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋራ ተካፈሉት” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አላቸው፦ “በብዙ ሀብት እጅግም ብዙ በሆነ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ እጅግም ብዙ በሆነ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በብዙ ብልጥግና፥ በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብዙ ብልጥግና በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፥ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ። |
እነርሱም በገለዓድ ምድር ብዙ የከብት መንጋ ስለ ነበራቸው በስተ ምሥራቅ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ተንጣልሎ ያለውን በረሓማ ምድር ሁሉ ያዙ።
ስለዚህ እግዚአብሔር የኢዮሣፍጥ መንግሥት በይሁዳ ላይ እንዲጸና አደረገ፤ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት ያመጡለት ስለ ነበረም እጅግ የበለጸገና የከበረ ሆነ፤
ንጉሥ ሕዝቅያስ እጅግ በለጸገ፤ ሕዝቡም ሁሉ አከበሩት፤ ወርቁን፥ ብሩን፥ የከበረ ዕንቊውን፥ ቅመማ ቅመሙን፥ ጋሻዎቹንና ሌሎቹንም ውድ የሆኑ ዕቃዎቹን የሚያኖርባቸው ዕቃ ግምጃ ቤቶችን ሠራ፤
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
ከዚያም በኋላ ዳዊትን ወራሪዎቹ ወዳሉበት እየመራ አደረሰው። ወራሪዎቹም በየቦታው ተበታትነው በመብላትና በመጠጣት ተድላ ደስታ በማድረግ ላይ ነበሩ፤ ከፍልስጥኤምና ከይሁዳ ያገኙት ምርኮ እጅግ ብዙ ነበር፤
እናንተ በምትሉት ነገር ማንም አይስማማበትም! ወደ ኋላ ቀርቶ ጓዝ ሲጠብቅ የቈየውም ሆነ ወደ ጦርነት የዘመተው ሁሉም የተገኘውን ምርኮ እኩል መካፈል አለበት” ሲል መለሰላቸው።