Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 17:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህ እግዚአብሔር የኢዮሣፍጥ መንግሥት በይሁዳ ላይ እንዲጸና አደረገ፤ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት ያመጡለት ስለ ነበረም እጅግ የበለጸገና የከበረ ሆነ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ መላው ይሁዳም ስጦታ ለኢዮሣፍጥ አመጣለት፤ ከዚህ የተነሣም ታላቅ ብልጽግናና ክብር አገኘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ስለዚህም ጌታ መንግሥቱን በእጁ አጸና፤ ይሁዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢዮሣፍጥ አመጣ፤ እጅግም ብዙ ሀብትና ክብር ሆነለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ቱን በእጁ አጸና፤ ይሁ​ዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ አመጣ፤ እጅ​ግም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ሆነ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸና፤ ይሁዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢዮሳፍጥ አመጣ፤ እጅግም ብዙ ብልጥግናና ክብር ሆነለት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 17:5
24 Referencias Cruzadas  

አብራም ብዙ እንስሶች፥ ብዙ ብርና ወርቅ ያለው ሀብታም ሰው ነበረ።


ወደ እርሱም የሚመጡት ሁሉ የብርና የወርቅ፥ የልብስ፥ የጦር መሣሪያዎች፥ የሽቶ፥ የፈረሶችና የበቅሎዎች ስጦታዎችን ያመጡለት ነበር፤ ይህም በየዓመቱ የሚደረግ ነበር።


በግዛቱም ዘመን ሁሉ በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፥ የሊባኖስ ዛፍ ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅለው ሾላ ይቈጠር ነበር፤


የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፥ ከዚያም አልፎ እስከ ግብጽ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር።


በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በኢየሩሳሌም ወርቅና ብር ከመብዛቱ የተነሣ እንደ ድንጋይ ተራ ነገር ነበር፤ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅል ሾላ ዛፍ ይቈጠር ነበር።


የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በሀብት በበለጸገና ዝነኛ በሆነ ጊዜ የእርሱና የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ቤተሰብ በጋብቻ እንዲተሳሰሩ አደረገ፤


ብዙ ሰዎች ለእግዚአብሔር መባን፥ ለንጉሥ ሕዝቅያስ ደግሞ ገጸ በረከትን ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሕዝቦች ሁሉ ሕዝቅያስን ከፍ ባለ አክብሮት ተመለከቱት።


በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፥ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅል ሾላ ይቈጠር ነበር።


እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት።


እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ የቤት ሠሪዎች ድካም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ የከተማ ጠባቂዎች ትጋት ከንቱ ነው።


ልጆችህ ቃል ኪዳኔንና የምሰጣቸውን ትእዛዞች ከጠበቁ ልጆቻቸው ከአንተ በኋላ ለዘለዓለም ይነግሣሉ።”


በዚህ ዐይነት በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ ነገሥታት መባን ያመጡልሃል።


የተርሴስ ደሴቶች ነገሥታት ስጦታ ያቅርቡለት፤ የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያምጡለት።


መፈራት ለሚገባው ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ተስላችሁ የተሳላችሁትን ስእለት ፈጽሙ፤ እናንተ በቅርብ ያላችሁ ሕዝቦች መባ አምጡለት።


መንግሥት የሚጸናው በፍትሕ ስለ ሆነ ክፉ ሥራ በመሪዎች ዘንድ የተጠላ ነው።


ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር ሆኖ አዩት፤ ተደፍተውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፥ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት።


እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤


ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብር የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ እርሱ ራሱ ከተቀበላችሁት መከራ ያድናችኋል፤ ይደግፋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።


ነገር ግን አንዳንድ ሥርዓተ አልባዎች “አሁን ይህ ሰው እኛን ለማዳን ይችላል?” ተባባሉ፤ እርሱንም በመናቅ ምንም ዐይነት ገጸ በረከት ሳያመጡለት ቀሩ። ሳኦል ግን ዝም አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos