ኢያሱ 21:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ የቀሩት የቀዓት ጐሣ ከግጦሽ ምድራቸው ጋር በድምሩ ዐሥር ከተሞች ተረከቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ዐሥር ከተሞች ሁሉ ከነመሰማሪያዎቻቸው ለተቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ተሰጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸው ጋር ዐሥር ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰማርያቸው ጋር ዐሥር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰምርያቸው ጋር አሥር ናቸው። |
የጌርሾን ጐሣ የሆነው ሌላው የሌዋውያን ወገን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ከምሥራቅ ምናሴ ግዛት ተከፍለው የተሰጡት ሁለት ከተሞች በባሳን ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ጎላን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር በዔሽተራ ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ናቸው፤